2ኛው የኢትዮጵያ ወጣቶች ኦሎምፒክ ጨዋታዎች የአትሌቲክስ ውድድሮች ነገ ይጀመራል

#

ጥቅምት 18/2018 ዓ.ም

2ኛው የኢትዮጵያ ወጣቶች ኦሎምፒክ ጨዋታዎች የአትሌቲክስ ውድድር ነገ በአዲስ አበባ ከተማ በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ይጀመራል ።

“የወጣቶች ኦሊምፒክ ውድድር ለሀገር ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል ከጥቅምት 15 እስከ 23/ 2018 ዓ.ም በሚካሄደው 2ኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ ጨዋታዎች ነገ የአትሌቲክስ ውድድሮች 185 ሴቶች፣ 187 ወንዶች በድምሩ 372 አትሌቶች ይሳተፋሉ።

ነገ በሚጀምረው ውድድር ላይ የሴቶች 3ሺ ሜትር የፍፃሜ ውድድርን ጨምሮ ሌሎች የማጣሪያ እና የፍፃሜ ውድድሮች ይካሄዳሉ ።

በውድድሩ ላይ ሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የሚሳተፋ ሲሆን ከነገ ጀምሮ እስከ ጥቅምት 23/2018 ዓ.ም ይካሄዳል ።

2ኛው የኢትዮጵያ ወጣቶች የኦሎምፒክ ጨዋታዎች በ19 የስፖርት ዓይነቶች የሚካሄድ ሲሆን ባሳለፍነው ሳምንት ቅዳሜ 15/2018 ዓ.ም በአዲስአበባ ስቴዲየም በድምቀት መጀመሩን የሚታወስ ነው።

Categories: Uncategorized