በትግራይ ክልል ሲሰጥ የነበረው የህፃናት አትሌቲክስ የክትትልና ግምገማ ተጠናቀቀ ።

#

ጥቅምት 18/2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በመቀለ ከተማ በተመረጡት ትምህርት ቤቶች ሲካሄድ የነበረው
የህፃናት አትሌቲክስ (Kid’s Athletics ) የክትትልና ግምገማ መርሀግብር ተጠናቀቀ።

ከአፄ ዮሐንስ አንደኛ ጀረጃ ትምህርት ቤት በተጨማሪ በኩሓ በመቀለ ዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ ስር የተቋቋመው ዓይናለም ት/ቤት የታዳጊ ሕፃናት(Kids) አትሌቲክስ ስልጠና በተጠናከረ ሁኔታ የተካሄደ ሲሆን የክትትልና ግምገማ ተግባር ተከናውኗል ።

ከት/ቤቱ ርዕሰ መምህር ፣የትግራይ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል፣
ከወላጅ ተወካዮች እንዲሁም ከአሰልጣኞች ጋር በመሆን አሁን ባለውና ወደፊት በሚሰሩት ተግባራት ላይ ከፌዴሬሽኑ ከፍተኛ የስልጠና ባለሙያ አቶ ተስፋዬ ይፍሩ ጋር ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጓል።

በትምህርት ቤቱ በጀት ለሰልጣኝ ታዳጊ ህጻናት የትጥቅ ድጋፍ የተደረገ ሲሆን የሕፃናቱን የመሥራት ፍላጎት ከመጨመሩም ባሻገር ለሌሎችም ተመኩሮ በመሆኑ ምስጋና ቀርበላቸዋል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የህፃናት አትሌቲክስ ተግባር አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።

Categories: Uncategorized