ታህሳስ 04/2018 ዓ.ም
1ኛው የኢትዮጵያ 10 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ለመጀመሪያ ጊዜ በትግራይ ክልል መቀለ ከተማ ነገ ታህሳስ 5/2018 ዓ.ም. በመቀለ ከተማ ይካሄዳል ።
ፌዴሬሽኑ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የኮሚኒኬሽን ንኡስ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ቢኒያም ምሩፅ፣የትግራይ ክልል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኪዳኔ
እና የፌዴሬሽኑ
ከፍተኛ የውድድር ባለሙያ አቶ ብስራት ለጥይበሉ እ በጋራ በመሆን ከአሰልጣኞች ፣ቡድን መሪዎች ፣የአትሌቲክስ ዳኞች፣ከፀጥታ አካላት እና ከውድድሩ ባለድርሻ አካላት ጋር በውድድሩ ቅድመ ዝግጅት ዙሪያ በመቀለ ከተማ ውይይት አድርጓል
የዉድድሩ ዓላማ
ለክልልና ከተማ አስተዳደ፣ ክለብ ፣ተቋማትና፣ የግል ተወዳዳሪ አትሌቶች የውድድር ዕድል ለመፍጠርና ፣ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት፤አትሌቶችን በሽልማት ለማበረታት አላማ ያደረገ መሆኑንና እስከአሁን በአጠቃላይ 80 አትሌቶች ለመወዳደር የተመዘገቡ ሲሆን ምዝገባው እየቀጠለ እንደሆነ ተጠቁመዋል ።
ውድድሩን ለማካሄድ 40 ዳኞች የተመደቡ ሲሆን ለአሸናፊ አትሌቶች
ሽልማት የሚሰጥ ሲሆን የመቀለ ነዋሪዎች አትሌቶችን እንዲያበራታቱ ተጠይቀዋል ።





