ታህሳስ 12/2018 ዓ.ም

በሳምንቱ መጨረሻ ላይ በተካሄዱ የጎዳና ላይ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ተቀዳጅቷል ።

በሕንድ ኮልኮታ የታታ ስቲል የ25 ኪሎሜትር ውድድር አትሌት ደጊቱ አዝመራው አሸንፋለች ።

አትሌቷ እርቀቱ ለማጠናቀቅ 1:19:36 የወሰደባት ሲሆን፣አትሌት ሱቱሜ አሰፋ ሁለተኛ ፤አትሌት መሰለች አለማየሁ ሶስተኛ በመሆን አሸንፈዋል ።

በውድድሩ ላይ የተሳተፉት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አትሌት ኩፍቱ ጣሂር ፤ አትሌት ዘመኗ ደምለው እና አትሌት ነፃነት ታፈረ ከአራት እስከ ስድስት ያለውን ደረጃ በመያዝ ውድድራቸውን አጠናቀዋል።

አትሌት ጋዲሴ ደምሴ የታይፔ ማራቶንን በ2:24:17 የቦታውን ክብረወሰን በማሻሻል አሸንፋለች ።

ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ትርፌ በየነ በ2:24:19 በመግባት ሁለተኛ ወጥታለች።

በሌላ በኩል በጓንግዙ ማራቶን አትሌት አፈወርቅ መስፍን በቀዳሚነት አሸንፏል ።

አትሌት አፈወርቅ እርቀቱን ለማጠናቀቅ 2:12:23 ወስዶበታል።

በሴቶች አትሌት ቤተልሔም አፈንጉስ በ2፡27.52 ሁለተኛ ስትወጣ አትሌት ጫልቱ ጭምዴሳ በ2፡31.37 ሦስተኛው ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።

Categories: Uncategorized