2ኛው የኢትዮጵያ ወጣቶች ኦሎምፒክ ጨዋታዎች የአትሌቲክስ ውድድር ዛሬ ተጀምሯል ።
#########################
የመጀመሪያ ቀኑን የያዘው 2ኛው የኢትዮጵያ ወጣቶች ኦሎምፒክ ጨዋታዎች የአትሌቲክስ ውድድር ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ በተለያዩ የፍፃሜ እና የማጣሪያ ውድድሮች ተጀምሯል ።
የሴቶች 3ሺ ሜትር ፍፃሜ ውድድር ውጤት :-
1ኛ ኤልሳቤጥ አማረ – አማራ ክልል-9:34.36
2ኛ ትርንጎ ታደሰ -አዲስአበባ – 9:35.21
3ኛ ዮርዳኖስ ጥጋቡ-ትግራይ -9:41.48
የአትሌቲክስ ውድድሮች ላይ 185 ሴቶች፣ 187 ወንዶች በድምሩ 372 አትሌቶች የሚሳተፉ ይሆናሉ።
ውድድሩም ነገም በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ የሚቀጥል ይሆናል።