መረጃ !
ለክልሎች ፣ከተማ አስተዳደሮች፣ክለቦችና ተቋማት :-
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን 43ኛው ጃንሜዳ ኢንተርናሽናል ሀገር አቋራጭ ውድድር በልዩ እና ታላቅ ድምቀት ለማካሄድ ከፍተኛ ዝግጅት በማድረግ ላይ ይገኛል።
ውድድሩ የሚካሄድበት ቀን ህዳር 07/2018 ዓ.ም እንደነበር ይታወቃል ።
ሆኖም ግን በአሜሪካ ፍሎሪዳ የሚካሄደው 46ኛው የዓለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮና ቀን መቅረብና ለቪዛ ፕሮሰስ በቂ ጊዜ በማስፈለጉ ምክንያት ሻምፒዮናው ወደ ጥቅምት 30/2018 ዓ.ም መቀየሩን እያሳወቅን ከወዲሁ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ በአክብሮት እንገልፃለን ።