ዛሬ በተካሄዱ ውድድሮች ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች አሸነፉ
#
ጥቅምት 16/2018 ዓ.ም
በቫሌንሽያ ግማሽ ማራቶን የወንዶች ውድድር በአትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ አሸናፊነት ተጠናቋል።
አትሌት ዮሚፍ ርቀቱን ለማጠናቀቅ 58:02 ሰዓት ወስዶበታል ።
በሴቶች አትሌት ፎትየን ተስፋይ በ 65:05 2ኛ ደረጃ ይዛ ውድድሯን አጠናቃለች።
በሌላ በኩል በ42ኛው የፍራንክፈርት ማራቶን በወንዶቹ አትሌት በላይ አስፋው አሸናፊ ሆኗል።አትሌቱ ርቀቱን ለማጠናቀቅ 2:06:16 ሰዓት ፈጅቶበታል።
ሌሎች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ተሬሳ ቤኩማ እና ሹራ ቂጣታ 2ኛ እና 3ኛ ደረጃ ይዘው ውድድሩን አጠናቀዋል።
በሴቶች አትሌት ቡዜ ድሪባ 2:19:34 በመግባት የግል ምርጥ ሰዓቷን አስመዝግባ አሸንፋለች።
በሊዝበን ግማሽ ማራቶን በሴቶች አትሌት ጫልቱ ዳዲ ሁለተኛ ስትወጣ በወንዶች አትሌት ሚኪያስ ባረጋ በተመሳሳይ ሁለተኛ ደረጃ ይዞ አጠናቋል።
በሻንግሀይ የ10 ኪሎሜትር የጎዳና ላይ ውድድር አትሌት አስማረች አንሊ በ31፡10 አሸንፋለች።
ትላንት በተደረገ የሊዝበን ማራቶን በሴቶች ውድድር አትሌት አበበች አፈወርቅ በ2:29.00 በመግባት ማሸነፏ የሚታወስ ነው።
ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት አስማሬ በየነ በ2:29:09 ሁለተኛ ወጥታለች።
በወንዶች ጋዲሳ ብርሀኑ ሁለተኛ ልመንህ ጌታቸው ሦስተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።
በአየርላንድ ደብሊን ማራቶን አትሌት ኤቢሴ አዱኛ በ2:26.28 አሸንፋለች።
አትሌት ቀና ግርማ ሁለተኛ ስትወጣ አትሌት አፀደ ባይሳ 2:27:12 ሦስተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።
በወንዶች ማናዞት ስዩም በ2:09:09 ሁለተኛ ወጥቷል።






