የህፃናት አትሌቲክስ (Kids Athletics ) በመቀለ ከተማ የስልጠና ሂደት ምልከታ ተካሄደ

#

ጥቅምት 16/2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በእቅድ ውስጥ አካትቶ ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል አንዱ የህፃናት አትሌቲክስ (Kid’s Athletics ) የስልጠና ሂደታቸውን ምልከታ ማድረግ ይገኝበታል ።

በዚህም መሰረት ፌዴሬሽኑ በትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በመቀለ ከተማ አፄ ዮሐንስ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት በሕፃናት አትሌቲክስ ታቅፈው የሚሰለጥኑትን የስልጠና ሂደታቸውን ምልከታ አድርጓል ።

የኢ/አ/ፌ/ የስልጠና ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ተስፋዬ ይፍሩና የትግራይ አትሌቲክስ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል መምህርት ስምረት ክፍላይ ክትትል እና ግምገማ በመቀለ ከተማ አካሂደዋል ።

በተጨማሪም አሰልጣኞቹ በእቅዳቸው ዙሪያ፣በሴፍ ጋርዲግ ሕፃናቱ ያለምንም ተፅንኖ ስልጠናቸውን መቀጠል እንዳለባቸው በባለሙያው ገለፃና ማብራሪያ ተደርጎላቸዋል።

በመጨረሻም በኢ/አ/ፌ/በባለሙያዎችና በአገራችን ታዋቂ አሰልጣኞች በጋራ የተዘጋጀውን የታዳጊ ሕፃናት አትሌቲክሰ ማሰልጠኛ ማንዋል መፅሀፍ ለአሰልጣኞ በኢ/አ/ፌ/ የስልጠና ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ተሰፋየ ይፍሩ እና የትግራይ አትሌቲክስ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል መምህርት ስምረት ክፍላይ ጋራ በጋራ ተበርክቷል ።

ፌዴሬሽኑ የህፃናት አትሌቲክስ ድጋፍ እና ክትትል ተግባር አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል ።

Categories: ዜና