በጃፓን ቶኪዮ የግማሽ ማራቶን አትሌት ሰለሞን ባረጋ አሸነፈ።

######################

ጥቅምት 9/2018 ዓ.ም

በጃፓን ቶኪዮ በተካሄደው የግማሽ ማራቶን ውድድር አትሌት ሰለሞን ባረጋ አሸንፈዋል ።

አትሌት ሰለሞን ርቀቱን ለማጠናቀቅ 1:01.21 ወስዶበታል።

በሴቶች ምድብ አትሌት መስከረም ማም ሦስተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።

በሌላ ዜና በአምስተርዳም ማራቶን ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች አሸንፈዋል ።

በሴቶች ውድድር አትሌት አይናለም ደስታ በ2 :17.37 በመግባት የግል ምርጥ ሰዓቷን አስመዝግባ አሸንፋለች።

አትሌት ብርቱካን ወልዴ 2ኛ ደረጃን ይዛ ስታጠናቅቅ አትሌት መቅደስ ሽመለስ 3ኛ ደረጃን ይዛ ፈፅማለች ።

በወንዶች የባለፈው ዓመት አሸናፊ አትሌት ጸጋዬ ጌታቸው 2ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል፡፡

አትሌት ጌታነህ ሞላ 3ኛ ደረጃን ይዞ ውድድሩን ጨርሰዋል ።

የኬንያዊውን አትሌት ጂዮፍሪ ኪብቹምባ ውድድሩን በአንደኝነት አጠናቋል፡፡

Categories: Uncategorized