29ኛው የፔፕሲ አዲስ አበባ የ30 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር በመቻል አጠቃላይ አሸናፊነት ተጠናቀቀ

##########################

ጥቅምት 9/2018 ዓ.ም

የአዲስአበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በእቅድ ይዞ ከሚያከናውናቸው ውድድሮች መካከል አንዱ የሆነው 30 ኪ.ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ተካሄደ ።

ውድድሩን በሴቶች አትሌት ረድኤት ዳንኤል በወንዶች አትሌት አበባው ደሳለኝ አሸነፋ።

መነሻ እና መድረሻውን በአዲስ አበባ ሰሚት አደባባይ ባደረገው በሴቶች አትሌት ረድኤት ዳንኤል በቀዳሚነት አጠናቀቀች ።

አትሌት ሲጫሌ ደረሰ ሁለተኛ አትሌት መሠረት ፍላቴ ሦስተኛ ደረጃን በመያዝ ፈፅመዋል።

በወንዶቹ ውድድር አትሌት አበባው ደሳለኝ ከመቻል አሸንፏል።

አትሌት አስራር ሀይዲን እና አትሌት ቶልቻ ተፈራ በቅደም ተከተል ሁለተኛ እና ሦስተኛ ወጥተዋል

ውድድሩን መቻል ስፖርት ክለብ በሁለቱም ፆታዎች አሸናፊ ሆኖ አጠናቋል ።

ውድድር ከ10 ክለቦች የተውጣጡ ከ180 በላይ አትሌቶች ተካፍለዋል።

በውድድሩ ከአንድ እስከ ስድስት የወጡ አትሌቶች የገንዘብ እና ሠርተፊኬት ተበርክቶላቸዋል ።

በውድድሩ ላይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ዶክተር ትዕዛዙ ሞሴ፣ የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አትሌት መልካሙ ተገኝ፣የአዲስአበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ።

l

Categories: Uncategorized