በስሎቬኒያ ሉቡሊያና ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ፆታ ድል ተቀዳጅቷል
########################
በሱሎቬኒያ ሉቡሊያና ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ፆታ ድል ተቀዳጅቷል ።
በወንዶች ውድድር አትሌት ሃፍታሙ አባዲ በ2:06:52 በመግባት በቀዳሚነት አጠናቋል።
በውድድሩ ላይ የተሳተፈው ኢትዮጵያዊ አትሌት ከማል ሁሴን ሦስተኛ ወጥቷል።
በሴቶች አትሌት ትግስት ገዛኸኝ በ2:22:46 በመግባት በአንደኝነት አሸንፋለች።