አትሌት መሠረት ደፋር በአሜሪካ ዋሺንግተን ዲሲ ሽልማት ተበረከተላት።
########################
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት አትሌት መሠረት ደፋር አሜሪካ ዋሺንግተን ዲሲ ላይ የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ በአትሌቲክሱ ላበረከተቹ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሽልማት ተበርክቶለታል ።
አትሌት መሠረት ደፋር በዓለም አትሌቲክስ የዓመቱ ኮከብ አትሌት ምርጫን በሴቶች ዘርፍ ያሸነፈች የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊት ናት፡፡
አትሌቷ በሩጫ ዘመኗ ያስመዘገበችው ስኬት ለተተኪ አትሌቶች ምሳሌ የሚሆን ነው።
የኦሊምፒክ እና የአለም ሻምፒዮኗ መሠረት የአገር ፍቅር፣ የቁርጠኝነት፣ የትጋት፣ ከጽናትና ተምሳሌት ናት ።
በሽልማት መርሀግብሩ ላይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን፣የቀድሞ የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር አትሌት ደራርቱ ቱሉ፣ የአሜሪካ ሴናተሮች፣ ከንቲባዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ።
ከአትሌት መሠረት በተጨማሪ በየአመቱ ስኬትንና የላቀ ስራ የሰሩ ልዩ ተሸላሚዎች ከኪነጥበብ፣ ከቢዝነስ ዘርፍ ተመርጠው ላደረጉት በጎ አስተዋፅኦ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል ።
በዘንድሮ የሽልማት መርሀግብሩ ላይ በአትሌቲክሱ የኦሊምፒክ እና ዓለም ሻምፒዮና አሸናፊ አትሌት መሠረት ደፋር በዓለም መድረክ የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ በአለም አደባባይ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ ማድረጓን ተከትሎ ነው የተበረከተላት ።
አፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ እስካሁን ለአራት ጊዜያት የተካሄደ ሲሆን በ2019 ረዳት ኮሚሽነር አትሌት ደራርቱ ቱሉ፣ በ2021 አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ፣ በ2022 አትሌት ቀነኒሳ በቀለ፣ በ2023 የዲባባ ቤተሰብና አትሌት ስለሺ ስህን እና በ2024 አትሌት ትዕግስት አሰፋና ጉዳፍ ፀጋይ ተሸላሚ የሆኑ የኢትዮጵያ ጀግና ልጆች ናቸው ።