አትሌት ሃዊ ፈይሳ የቺካጎ ማራቶን አሸነፈች
########################
አትሌት ሃዊ ፈይሳ 47ኛውን የቺካጎ ማራቶን አሸነፈች።
አትሌት ሃዊ ርቀቱን ለማጠናቀቅ 2:14.56 ሰዓት ወስዶባታል ።
ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊ አትሌት መገርቱ አለሙ በ2:17:18 በመግባት 2ኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች።
በወንዶች ኢትዮጵያዊያኑ አትሌቶች አትሌት ሁሰዲን መሀመድ እና አትሌት ሰይፉ ቱራ 5ኛ እና 6ኛ ደረጃን በቅደም ተከተል ይዘዋል ።
ኡጋንዳዊው አትሌት ጃኮብ ኪፕሊሞ በ2:02:23 አሸንፏል።
ኬንያውያኑ አሞስ ኪፕሩቶ እና አሌክስ ማሳይ ሁለተኛና ሦስተኛ ሆነው ውድድሩን ፈፅመዋል።