በ20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በተመዘገበው ውጤት የኢትዮጵያ ህዝብን ይቅርታ እንጠይቃለን:- ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን

#################################

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን በቶኪዮ ጃፓን በተካሄደው 20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና አስመልክቶ ለመገናኛ ቡዙሃን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ፕሬዝደንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን በጃፓን ቶኪዮ በተካሄደው 20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተመዘገበው ደካማ ውጤት የተከፋውን የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ ጠይቀዋል ።

ፕሬዝደንቱ በተጨማሪም ለሌላ ሻምፒዮናዎች የተለየ ዝግጅት በማድረግ ፣የተሻሻለ ደንብ እና መመሪያ በማውጣት እና ብሄራዊ ቡድን በሟቋቋም እና ሪፎርም በማድረግ ህዝባችንን እንክሳለን ብሏል።

በሻምፒዮናው ኢትዮጵያ በ35 አትሌቶች የተወከለች መሆንዋንና በሁለት ብር እና በሁለት የነሃስ ሜዳልያ የተመዘገበ ውጤት ያልተጠበቀ መሆኑን ያነሱ ሲሆን በጋራ መስራት እንደሚያስፈልግ ፕሬዝዳንቱ አንስቷል ።

የፌዴሬሽኑ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የኢትዮጵያ አትሌቶች ማህበር ፕሬዘዳንት ሌተናል ኮነሬል አትሌት የማነ ፀጋይ በበኩላቸው ለተመዘገበው ውጤት ማዘናቸው ያነሱ ሲሆን ፌዴሬሽኑ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለውጥ ለማምጣት እንደሚስራ ያነሱ ሲሆን፣የሚስተዋሉ ሰፋፊ ችግሮችን ለመፍታት እና የማኔጀሮች እና አሰልጣኞች ጣልቃ ገብነት ለመፍታት ከፍተኛ ጥረት ይደረጋል ብሏል።

የፌዴሬሽኑ የስልጠና ክፍል ዳይሬክተር ኢንስትራክተር ሳሙኤል ብርሃኑ በሻምፒዮናው የስልጠና ዝግጅት ክፍተት እንደነበርና አንድ አንድ አሰልጣኞች እና አትሌቶች ፍቃደኝነት አናሳ መሆንና እቅዳቸውን በሚፈለገው ስዓት አለማስገባት ተስተውሏል ብሏል።

የሻምፒዮናው የቴክኒክ ቡድን መሪ አቶ አሰፋ በበኩላቸው የተመዘገበው ውጤት አናሳ መሆኑን ጠቁመው በዝርዝር የቴክኒክ ጉዳዮች አንስተዋል።

የፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮሐንስ እንግዳ እና የሻምፒዮናው የቴክኒክ ምክትል ቡድን መሪ አትሌት አሸብር ደምሴ በተጨማሪ መግለጫ ሰጥተዋል።

Loading

Categories: Uncategorized