የአዲስአበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን 43ኛው ጠቅላላ ጉባኤውን አካሄደ

#

መስከረም 18/2018 ዓ.ም

የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር አትሌቲክስ ፌዴሬሽን 43ኛው ጠቅላላ ጉባኤውን በቫይብስ ሆቴል ዛሬ አካሂዷል ።a as

ጉባኤው በአዲስአበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አትሌት መልካሙ ተገኝ መክፈቻ ንግግር የተጀመረ ሲሆን የ2017 ዓ.ም ዝርዝር የስራ አፈፃፀም ሪፖርት በፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት ኃላፊ ወይዘሮ እታፈራሁ ገብሬ ቀርበዋል።

በተጨማሪም የ2017 ዓ.ም የፋይናንስ እና የኦዲት አፈፃፀም ሪፖርት ለጉባኤተኛው የቀረበ ሲሆን በቀረበው ሪፖርት ላይ ሰፊ ውይይት ሲካሄድ፣ወይዘሮ እታፈራሁ ገብሬ የ2018 ዓ.ም እቅድና በጀት አቀርበዋል ።

በጉባኤው ላይ የተጓደሉት የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ላይ የሟሟያ ምርጫ የተደረገ ሲሆን የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ክለቦችና ተቋማት የእውቅናና ሽልማት መርሀግብር በማበርከት ጉባኤው ተጠናቀዋል ።

በጉባኤው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን ፣የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ዶክተር ትዕዛዙ ሞሴ እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ።

Loading

Categories: Uncategorized