በ10ሺህ ሜትር ሴቶች የፍፃሜ ውድድር ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ሜዳሊያ አገኘች።
#########################
በ10ሺ ሜትር የሴቶች ፍፃሜ ውድድር አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ በ30:39.65 ለኢትዮጵያ የነሀስ ሜዳልያ አስገኘች።
በውድድሩ የተካፈሉት አትሌት እጅጋየሁ ታዬ 30:55.52 በመግባት 5ኛ ፤አትሌት ፎትየን ተሰፍይ 31:21.67 በመግባት 8ኛ ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል።
ውድድሩ ቢትሪስ ቼቤት በ30:37.61 በሆነ ስዓት በመግባት አሸንፋለች ።