የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ቡድን ሦስተኛው ተጓዥ ዛሬ ማምሻውን ወደ ቶኪዮ ተጉዟል
ከመስከረም 3-11/2018 ዓመት የሚካሄደው 20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ቡድን ዛሬ ምሽት 4:35 ወደ ጃፓን ቶኪዮ አቅንቷል ።
የፌዴሬሽኑ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና አቃቤ ነዋይ ወ/ሮ አበባ ዮሴፍ፣ የፌዴሬሽኑ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ወ/ሮ ሳራ ሃሰን ፣የፌዴሬሽኑ ም/ጽቤት ሃላፊ ወ/ሮ ማስተዋል ዋለልኝ እና የተሳትፎና ውድድር ንዑስ የስራ ሂደት መሪ ተወካይ አቶ ብስራት ለጥይበሉ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተገኝተው የልዑክ ቡድኑን ሸኝተዋል ።
መልካም ጉዞ !
መልካም እድል ለአትሌቶቻችን !