የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ቡድን የሁለተኛው ተጓዥ ዛሬ ማምሻውን ወደ ጃፓን ቶኪዮ አመራ።

ዻጉሜ 05/2017 ዓ.ም

በ20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ቡድን ዛሬ ምሽት 4:35 ወደ ጃፓን ቶኪዮ አቅንቷል ።

የኢትዮጵያ አትሌቲክ ፌዴሬሽን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ኢንጅነር ጌቱ ገረመው ፣የፌዴሬሽኑ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና አቃቤ ነዋይ ወ/ሮ አበባ ዮሴፍ፣ የፌዴሬሽኑ ም/ጽቤት ሃላፊ ወ/ሮ ማስተዋል ዋለልኝ እና የተሳትፎና ውድድር ንዑስ የስራ ሂደት መሪ ተወካይ አቶ ብስራት ለጥይበሉ በቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተገኝተው የልዑክ ቡድኑን ሸኝተዋል ።

🛫መልካም ጉዞ !

🇪🇹 መልካም እድል ለአትሌቶቻችን !

Loading

Categories: Uncategorized