ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በኢዩጂን ዳይመንድ ሊግ ውድድር
ትናንት በኢዩጂን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የተሳተፉበት የወንዶች 10 ሺህ ሜትር ፣የሴቶች 5 ሺህ ፣800 ሜትር እና 1500 ሜትር ውድድር ተካሂዷል ።
በወንዶች 10ሺህ ሜትር ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከ 1-3 በመውጣት ድል ተቀዳጅቷል ።
አትሌት ቢኒያም መሀሪ ውድድሩን በ 26:43.82 በመግባት ሲያሸንፍ ፣አትሌት በሪሁ አረጋዊ 26:43.84 በመግባት ሁለተኛ ሲወጣ
አትሌት ሰለሞን ባረጋ 26: 44.13 በሆነ ሰዓት ሶስተኛ ደረጃ ይዘዋል ።
በ5ሺህ ሴቶች ውድድር የፓሪስ ኦሎምፒክ የ5ሺ እና 10ሺ ሜትር ሻምፒዮናዋ ቢያትሪስ ችቤት የዓለም ክብረ ወሰንን በመስበር አሸንፋለች ።
አትሌት ቢያትሪስ ችቤት 13:58.06 በመግባት በአትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ ተይዞ የነበረውን የዓለም ክብረ ወሰን አሻሽላለች ።
በውድድሩ ላይ ኬንያዊቷ አትሌት ንጌቲች ሁለተኛ ስትወጣ አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ በ14:04.41 ሶስተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።
በ800 ሜትር ሴቶች ውድድር አትሌት ፅጌ ዱግማ 1:57.10 በመግባት በአንደኝነት አሸንፋለች ።
በ1500 ሜትር ውድድር ኬንያዊቷ አትሌት ፌዝ ኪፒዮጎን በ3:48.68 በመግባት በራሷ ተይዞ የነበረውን ክብረወሰን በማሻሻል አሸንፋለች።
በውድድሩ ላይ የተሳተፈችው አትሌት ድርቤ ወልተጂ በ3:51.44 በመግባት ሁለተኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቃለች ።
በሌላ ዜና በፈረንሳይ ናንሲ በተካሄደው የ800 ሜትር የሴቶች ውድድር አትሌትንግስት ጌታቸው 1:58.15 በመግባት ስታሸንፍ፣ በወንዶች ውድድር አትሌት ዮሐንስ ተፈራ 1:44.49 በመግባት ሶስተኛ ደረጃ በመያዝ ውድድሩን አጠናቀዋል።