54ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በታላቅ ድምቀት ተጠናቀቀ ።

ግንቦት 03/2017 ዓ.ም

ከሚያዝያ 28-ግንቦት 03/2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ሲካሄድ የቆየው 54ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በታላቅ ድምቀት ተጠናቀቀ።

በሻምፒዮናው ላይ 1379 አትሌቶች ፣31 ክለቦችና ተቋማት ፣ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ተሳትፈዋል ።

54ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በድምር ውጤት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 279 ነጥብ አንደኛ፣ መቻል 242 ነጥብ ሁለተኛ እንዲሁም ሸገር ሲቲ 143 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ በመያዝ ውድድራቸውን አጠናቀዋል ።

ዛሬ የተካሄዱ የፍፃሜ ውድድሮች :-

⏺️4X400 ሜትር ሪሌ ወንድ

ኢት/ኤሌትሪክ 3፡1051 1ኛ

ሸገር ሲቲ 3፡10.53 2ኛ

መቻል 3፡14.56 3ኛ

⏺️4X400 ሜትር ሴት

ኢት/ኤሌትሪክ 3፡37.38 1ኛ

ሃና አምሳሉ ሲዳማ ቡና 3፡41.25 2ኛ

ኢት/ንግድ ባንክ 3፡42.16 3ኛ

⏺️5000 ሜትር ወንድ

ኦሮ/ኮን/ኢንጅነሪግ 14፡12.51 1ኛ

ኢት/ኤሌትሪክ 14፡13.75 2ኛ

ኢት/ንግድ ባንክ 14፡14.57 3ኛ

⏺️4X100 ሜትር ወንድ

ሸገር ሲቲ 40.98 1ኛ

ኢት/ንግድ ባንክ 41.46 2ኛ

ጥሩነሽ ዲባባ 41.94 3ኛ

⏺️4X100 ሜትር ታ ሴት

ሲዳማ ቡና 46.00 1ኛ

ኢት/ኤሌትሪክ 47.24 2ኛ

ኢት/ንግ/ባንክ 48.19 3ኛ

⏺️ከፍታ ዝላይ ሴት

ፖች ኡመድ ኢት/ንግድ ባንክ 1.80 1ኛ

በፀሎት አለማየሁ መቻል 1.73 2ኛ

ሳራ ኛኘው መቻል 1.70 3ኛ

⏺️5000 ሜትር ሴት

የኔዋ ንብረት ኢት/ንግድ ባንክ 16፡06.87 1ኛ

ገመኔ ማሚቴ ኦሮ/ፖሊስ 16፡07.38 2ኛ

ዝይን አየልኝ ኢት/ኤሌትሪክ 16፡08.33 3ኛ

⏺️1500 ሜትር ወንድ

ሞሲሳ ስዩም ሸገር ሲቲ 3፡39.24 1ኛ

አዳህና ካሳይ ኢት/ንግድ ባንክ 3፡39.57 2ኛ

ወገኔ አዲሱ ኢት/ኤሌትሪክ 3፡40.66 3ኛ

⏺️1500 ሜትር ሴት

ሰላሌ ዩኒቨርስቲ 4፡11.30 1ኛ

ትዕግስት ግርማ መቻል 4፡11.99 2ኛ

ብርቱኳን ደጉ ኢት/ኤሌትሪክ 4፡12.24 3ኛ

በ54ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሪከርድ የሰበሩ

  1. በወንዶች በርዝመት ዝላይ ውድድር በ2005 ዓ.ም. በመከላከያ ክለብ  አትሌት ሊንጎ ኦባንግ  በ7.81 ሜትር በመዝለል ተይዞ የነበረውን ሪከርድ በ54ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ በሸገር ሲቲ ክለብ አትሌት ቡሊ መላኩ 8.13 ሜትር በመዝለል የአዲስ ሪከርድ ባለቤት ሆኗል/ች፡፡
  • በሴቶች በዲስከስ ውርወራ ውድድር በ2014 ዓ.ም. በኢት/ንግድ ባንክ ክለብ  አትሌት መርሃዊት ፀሐዬ በ45.40 ሜትር በመወርወር ተይዞ የነበረውን ሪከርድ በ54ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ በመቻል ክለብ አትሌት ዙርጋ ኡስማን 46.72 ሜትር በመወርወር የአዲስ ሪከርድ ባለቤት ሆኗል/ች፡፡
  • በወንዶች በዲስከስ ውርወራ ውድድር በ2014 ዓ.ም. በሲዳማ ቡና ክለብ  አትሌት ማሙሽ ታዬ በ45.09 ሜትር በመወርወር ተይዞ የነበረውን ሪከርድ በ54ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ በመቻል ክለብ አትሌት ቴዎድሮስ ቦጋለ 45.64 ሜትር በመወርወር የአዲስ ሪከርድ ባለቤት ሆኗል/ች፡፡
  • በሴቶች በአሎሎ ውርወራ ውድድር በ2014 ዓ.ም. በመቻል ክለብ  አትሌት ዙርጋ ኡስማን በ13.56 ሜትር በመወርወር ተይዞ የነበረውን ሪከርድ በ54ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ በመቻል ክለብ አትሌት ዙርጋ ኡስማን 13.67 ሜትር በመወርወር የአዲስ ሪከርድ ባለቤት ሆኗል/ች፡፡
  • በወንዶች በስሉስ ዝላይ  ውድድር በ2016 ዓ.ም. በኢት/ኤሌትሪክ ክለብ አትሌት ዶል ማች በ16.41 በመዝለል ተይዞ የነበረውን ሪከርድ በ54ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ክለብ አትሌት ዶል ማች 16.77 በመዝለል የአዲስ ሪከርድ ባለቤት ሆኗል/ች፡፡
  • በወንዶች በከፍታ ዝላይ  ውድድር በ2011 ዓ.ም. በሲዳማ ቡና ክለብ አትሌት ዳኘ ሌም በ2.10 በመዝለል ተይዞ የነበረውን ሪከርድ በ54ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ክለብ አትሌት ዶል ማች 2.11 በመዝለል የአዲስ ሪከርድ ባለቤት ሆኗል/ች፡፡
  • በሴቶች በስሉስ ዝላይ  ውድድር በ2016 ዓ.ም. በኢት/ንግድ ባንክ ክለብ አትሌት ፖች ኡመድ በ13.29 በመዝለል ተይዞ የነበረውን ሪከርድ በ54ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ክለብ አትሌት ፖች ኡመድ 13.35 በመዝለል የአዲስ ሪከርድ ባለቤት ሆኗል/ች፡፡
  • በሴቶች ከፍታ ዝላይ  ውድድር በ2011 ዓ.ም. በኢት/ንግድ ባንክ ክለብ አትሌት አርአያት ዲቦ በ1.76 በመዝለል ተይዞ የነበረውን ሪከርድ በ54ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ክለብ አትሌት ፖች ኡመድ 1.80 በመዝለል የአዲስ ሪከርድ ባለቤት ሆኗል/ች፡፡
  • በሴቶች ርዝመት ዝላይ  ውድድር በ2008 ዓ.ም. በመከላከያ ክለብ አትሌት ፖች ኡመድ በ5.83 ሜትር በመዝለል ተይዞ የነበረውን ሪከርድ በ54ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ክለብ አትሌት ፖች ኡመድ 6.21 ሜትር በመዝለል የአዲስ ሪከርድ ባለቤት ሆኗል/ች፡፡

54ኛዉ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የዋንጫ አሸናፊ

ተ.ቁፆታያስመዘገበዉ ነጥብደረጃክልል/ከተማአስተዳደር/ክለብ ፣ተቋም/
  1.    ቶች693ኛሲዳማ ቡና
1222ኛመቻል
1021ኛኢት/ንግድ ባንክ
  2.    ወንዶ1063ኛሸገር ሲቲ
1172ኛኢት/ንግድ ባንክ
1201ኛመቻል
  3.    አጠቃላይ ወ/1433ኛሸገር ሲቲ
2422ኛመቻል
2791ኛኢት/ንግድ ባንክ

በሻምፒዮናው ላይ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዲኤታ ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባየ፣የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን፣የፌዴሬሽኑ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ኢንጅነር ጌቱ ገረመው፣የፌዴሬሽኑ ምክትል ፕሬዚዳንት አትሌት መሠረት ደፋር፣ የፌዴሬሽኑ

የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት፣አንጋፋ አሠልጣኞችና አትሌቶችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ።

Loading

Categories: Uncategorized, ዜና