በሳምንቱ መጨረሻ በተለያዩ የአለም ክፍሎች በተደረጉ የጎዳና ላይ ውድድሮች ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች አሸንፈዋል።

ሚያዝያ 12/2017 ዓ.ም

በሳምንቱ መጨረሻ በተለያዩ የአለም ክፍሎች በተካሄዱ የጎዳና ላይ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ተቀዳጅተዋል ።

በቦስተን የ5 ኪሎሜትር ውድድር አትሌት ገላ ሀምበሴ 14 ደቂቃ ከ53 ሰከንድ በመግባት በአንደኝነት አሸንፋለች ።

በውድድሩ ላይ የተሳተፉት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ፣አትሌት ፅጌ ገብረሰላማ 4ኛ ፣አትሌት ለምለም ሀይሉ 5ኛ ደረጃን ይዘው ውድድራቸውን አጠናቀዋል ።

በሻናይ ግማሽ ማራቶን ውድድር አትሌት ፈታ ዘርአይ በቀዳሚነት አሸንፋለች ።

አትሌት ፈታ 1ሰዓት ከ06 ደቂቃ ከ36 ሰከንድ በመግባት የቦታውን ክብረወሰን በማሻሻል

ማሸነፍ ችላለች።

በሀር ቺንዶ ማራቶን በሴቶቹ አትሌት ብዙአለም ጨቅሌ አሸንፋለች።

አትሌቷ ርቀቱን ለማጠናቀቅ 2 ሰዓት ከ30ደቂቃ ከ33ሰከንድ ወስዶባታል።

ፀሐይ ገብሬ በስድስት ሰከንዶች ዘግይታ ሁለተኛ ወጥታለች።

በወንዶቹ አትሌት ሞላልኝ ፋንታሁን 2 ሰዓት ከ12 ደቂቃ ከ39 ሰከንድ ውድድሩን በማጠናቀቅ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል

ተጠባባቂው በአለም አትሌቲክስ የፕላቲንየም ደረጃ በተሰጠው 129ኛው ቦስተን ማራቶን በሴቶች ምድብ አትሌት ያለምዘርፍ የኃላው በ 2:18.06 በመግባት ፣ሶስተኛ ደረጃ በመያዝ ውድድርዋን አጠናቃለች ።

አትሌት ሻሮን ሎኬዲ በ2:17.20 በሆነ ስዓት በመግባት ስታሸንፍ፣ሄለን ኦብሪሪ ሁለተኛ ደረጃ ይዛለች።

አትሌት አማኔ በሪሶ 02:21.58 በሆነ ስዓት በመግባት አምስተኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቃለች ።

የቦስተን ማራቶን በወንዶች ምድብ ኬንያዊው አትሌት ጆን ኮሪር 2:04.45 በመግባት አሸንፈዋል ።

ኢትዮጵያዊ አትሌት ሙክታር እድሪስ አምስተኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቀዋል።

Categories: Uncategorized