የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለቦሬ አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል የስፖርት ትጥቅ ድጋፍ አደረገ ።
መጋቢት 07/2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለቦሬ አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል የስፖርት ትጥቅ ድጋፍ አድርጓል ።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ባለሙያዎች አቶ ይሄይስ ግርማ እና አቶ ዳንኤል ኪዳኔ በጋራ በመሆን ሰልጣኞች እና አሰልጣኞች በተገኙበት የስፖርት ትጥቁን አስረክበዋል ።
የቦሬ አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል አመራሮች እና አሰልጣኞች ፌዴሬሽኑ ላደረገላቸው ድጋፍ በማመስገን የስፖርት ትጥቁን ተረክቧል ።
ፌዴሬሽኑ ለቦቆጂ ፣ ለደብረብርሃን እና ለሀገረሰላም አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከላት ዓመታዊ የስፖርት ትጥቅ ማድረጉ የሚታወስ ነው።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስፖርት ትጥቅ ስርጭቱን አሁንም አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል ።



