የ2025 የሴኡል ማራቶን በሁለቱም ፆታ በኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸናፊነት ተጠናቀቀ።

መጋቢት 07/2017 ዓ.ም

የ2025 የሴኡል ማራቶን በሁለቱም ፆታ በኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸናፊነት ተጠናቀዋል ።

በወንዶች የ2025 ሴኡል ማራቶን አትሌት ሀፍቱ ተክሉ በ2:05.37 በመግባት በአንደኝነት አሸንፈዋል ።

በሴቶች ምድብ አትሌት በቀለች ጉደታ በ2:21.35 በአንደኛ ደረጃ ፣አትሌት ፍቅርተ ወረታ ሁለተኛ እንዲሁም አትሌት መስታውት ፍቅር ሶስተኛ ደረጃ በመያዝ ተከታትሎ በመግባት አሸንፈዋል ።

Categories: ዜና