በድል እንደምትመለሱ እና የአገራችን ሰንደቅዓላማ በዓለም አደባባይ ከፍ እንደምታደርጉ አልጠራጠርም :- ክቡር አቶ መኪዩ መሀመድ የኢ.ፌ.ድ.ሪ.ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ

መጋቢት 09/2017 ዓ.ም

ከማርች 21-23 በዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ቡድን ዛሬ እኩለ ሌሊት ወደ ቻይና ናንጂንግ አቅንተዋል ።

በቦሌ አለምአቀፍ አየር ማረፊያ ተገኝተው ሽኝት ያደረጉላቸው የኢ.ፌ.ድ.ሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር አቶ መኪዩ መሀመድ በድል እንደምትመለሱ እና የአገራችንን ሰንደቅዓላማ በአለም አደባባይ ከፍ እንደምታደርጉ አልጠራጠርም ፣የኢትዮጵያ ህዝብም አሸናፊነት ስለለመደ የተሰጣችሁን አደራ ተቀብላችሁ አኩሪ ድል እንደምታስመዘግቡ ባለ ሙሉ እምነት ነኝ ብሏል።

ሚኒስትሩ አክሎም መንግስት ለአትሌቲክሱ እድገት ልዩ ትኩረት በመስጠት እየሰራ መሆኑን በማስገንዘብ ስትመለሱ የጀግና አቀባበል እንደሚደረግላቸውም አሳስበዋል ።

ልዑክ ቡድኑ 12 አትሌቶች ፣2 አሰልጣኞች ፣

አንድ ቡድን መሪ፣አንድ ቴክኒክ ቡድን መሪ፣አንድ ከፍተኛ የህክምና ባለሙያ እና አንድ ፊዝዮቴራፒስት ያካተተ ነው።

የኢ.ፌ.ድ.ሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር አቶ መኪዩ መሀመድ፣የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን፣የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ዶክተር ትዕዛዙ ሞሴ፣ ኢንስትራክተር አድማሱ ሳጂ፣አቶ ቢኒያም ምሩፅ እና የኢትዮጵያ አትሌቶች ማህበር ፕሬዚዳንት እና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል አትሌት የማነ ፀጋይ ቦሌ አለምአቀፍ አየር ማረፊያ በመገኘት ልዑክ ቡድኑ በማበረታታት ሽኝት አድርጎላቸዋል ።

Categories: Uncategorized