ለሀገረ ሰላም አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል የስፖርት ትጥቅ ድጋፍ ተደረገ።
መጋቢት 05/2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በየዓመቱ ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል ለአትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከላት፣ፕሮጀክቶች፣ ለክልል እና ለከተማ አስተዳደሮች አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች የስፖርት አልባሳት ድጋፍ ማድረግ ነው ::
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሀገረ ሰላም አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል ዓመታዊ የስፖርት ትጥቅ ድጋፍ አድርጓል ።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የአትሌቲክስ ፣የስልጠና ፣ጥናትና ምርምር ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ጊዜ አድነው እና የፌዴሬሽኑ ሠራተኛ አቶ ገዙ ዘርየ በጋራ በመሆን ሰልጣኞች እና አሰልጣኞች በተገኙበት የስፖርት ትጥቁን አስረክበዋል ።
የሀገረ ሰላም አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል ዋና ስራአስኪያጅ አቶ ደሳለኝ ሀማጦ ለተደረገላቸው ድጋፍ በማመስገን የስፖርት ትጥቁን ተረክቧል ።
ፌዴሬሽኑ ለቦቆጂ እና ለደብረብርሃን አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከላት ዓመታዊ የስፖርት ትጥቅ ማድረጉ የሚታወስ ነው።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስፖርት ትጥቅ ስርጭቱን አሁንም አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል ።



