አትሌት ፅጌ ገብረሰላማ የሊዝበን ግማሽ ማራቶን አሸነፈች።
የካቲት 30/2017 ዓ.ም
በፖርቹጋል ሊዝበን በተካሄደው የግማሽ ማራቶን ውድድር አትሌት ፅጌ ገብረሰላማ የቦታውን ክብረወሰን በማሻሻል አሸንፋለች ፡፡
አትሌት ፅጌ ገብረሰላማ 1:04.21 በመግባት በአንደኝነት አሸንፋለች ።
ኬንያዊቷ አትሌት ሩዝ ቼፕንጌቲች 1:06.20 ሁለተኛ ደረጃ፣ ለስዊድን የምትሮጠው አትሌት አበባ አረጋዊ ሶስተኛ ደረጃ በመያዝ ውድድራቸውን አጠናቀዋል ።
