የቢሾፍቱ አለም አቀፍ የ10 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫን ውድድር አስመልክቶ ዛሬ በቢሾፍቱ አየር ሀይል ግቢ ውስጥ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል ።
መግለጫውን የሰጡት የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ ተቋማቸው አትሌቲክሱን ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን ገልጠዋል ።
አየር ኃይል የኢትዮጵያ ኩራት እንደመሆኑ መጠን ውድድሩን ካሁን በኃላ ቀጣይነት ባለው መልኩ እንደሚደረግ ነው ያስታወቁት ።
የኢትዮጵያ አየር ኃይል ጀግናው ሻምበል ምሩፅ ይፍጠር ጀምሮ በአትሌቲክሱ ትልቅ ተምሳሌት የሆነ ተቋም መሆኑን ያነሱት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን፣ የአየር ኃይል ክለብ መልሶ እንዲቋቋም ጠይቀዋል።
ፌዴሬሽኑ ውድድሩ አለማቀፍ ይዘት እንዲኖረው የሌላ አገር አትሌቶችን እንደሚጋብዝ የተናገሩት ፕሬዚዳንቱ ከሌሎች መሰል ውድድሮች በተሳትፎ ፤ በሽልማት ገንዘብ እና በሀይቅ ዙሪያ ቢሾፋቱ ላይ መካሄዱ ልዩ እንደሚያደርገው ገልፀዋል ።
90ኛ አመት የአየር ኃይል የምስረታ ቀን አስመልክቶ ለአየር ኃይል እድገት “በሙሉ አቅሜ እሮጣለሁ ” በሚል መሪ ሀሳብ በሚካሄደው ውድድር 25 ሺህ ተሳታፊዎች ይካፈሉበታል።
በቢሾፍቱ አለም አቀፍ የ10 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫን ውድድር ላይ ለሚካፈሉ አትሌቶች እና ክለቦች በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሆነ ሽልማት ተዘጋጅቷል ።
በመግለጫው የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ ፤ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን ፣የቢሸፍቱ ከተማ ከንቲባ አቶ አለማየሁ አሰፋ እና የኦሮሚያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጽ/ቤት ሀላፊ ኢንስትራክተር ሽመልስ ዳዊት ተገኝተዋል ።






