በናይጄሪያ አቡኩታ የአፍሪካ ከ18 እና 20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የተሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ቡድን የእውቅና እና ሽልማት መርሀግብር ተካሄደ

ሐምሌ 15/2017 ዓ.ም

በናይጄሪያ አቡኩታ ከተማ በተካሄደው የአፍሪካ ከ20 እና 18 ዓመት በታች ሻምፒዮና ላይ ለተሳተፋት እና አበረታች ውጤት ላስመዘገበው የአትሌቲክስ ልዑክ ቡድን የእውቅናና የሽልማት መርሀ ግብር ተከናወነ ፡፡

በውድድሩ ላይ አበረታች ውጤት ላስመዘገበው ልዑክ ቡድን የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቷል ።

በመርሀግብሩ ላይ የቡዱኑ መሪ ኢንስትራክተር አድማሱ ሳጂ ስለነበራቸው ቆይታ አብራርተዋል

ኢንስትራክተሩ በብዙ ችግር ውስጥ ተፈትኖ ጥሩ ውጤት ላመጡት የቡድኑ አባላትን አመስግነዋል ።

በተጨማሪም የቡድኑ ቴክኒክ ቡድን መሪ አቶ ጊዜ አድነው፣አሠልጣኝ መሰረት መንግሥቱ ፣በሻምፒዮናው የወርቅ እና ብር ሜዳልያ አሸናፊ እና በ1500 ወንዶች አትሌት ሳሙኤል ስለነበራቸው አጠቃላይ የውድድር ሁኔታ በስፋት አንስቷል።

በሻምፒዮናው የተሳተፈው በቸኛው ኢትዮጵያዊ ዳኛ ኢንስትራክተር ሳሙኤል ብርሃኑ ስለ ነበራቸው የውድድሩ የዳኝነት ቆይታ የተናገሩ ሲሆን ፌዴሬሽኑን ላደረገላቸው ድጋፍ ምስጋና አቅርቧል ።

በመጨረሻም የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን ለልዑክ ቡድኑ እንኳን ደህና መጣችሁ ያሉ ሲሆን ቡድኑ ያስመዘገበው ውጤት ጥሩ መሆኑን አንስተዋል ።

በተለይም ፌዴሬሽኑ በዕድሜ ተገቢነት ምርመራ ላይ የወሰደው ቆራጥ እርምጃ ለብዙ የአፍሪካ አገሮች በተሞክሮ ሊወሰድ የሚችል እንደሆነ ተናግሯል ።

ፕሬዚዳንቱ አክሎም በተተኪ አትሌቶች ላይ ፌዴሬሽኑ በትኩረት እንደሚሰራ በማንሳት ፣ለዓመታት ችግር ሁኖ የቆየው የትራክ እና የማዘውተሪያ ስፍራ እጥረት በአጭር ጊዜ ውስጥ ለመፍታት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተሰራ እንደሆነ አንስተዋል ።

ኢትዮጵያ በውድድሩ ላይ በ28 አትሌቶች የተሳተፈች ሲሆን 2 ወርቅ፣ 3 ብር እና 5 ነሃስ በአጠቃላይ 10 ሜዳልያዎችን አስመዝግባለች

Loading

Categories: Uncategorized