የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጋር በአትሌቲክሱ ልማት ዙሪያ በጋራ ለመስራት ተስማሙ።
የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጋር ” በአትሌቲክስ ልማት” ዙሪያ አብሮ ለመስራት ሰፊ ውይይት አካሂደዋል።
ክቡር የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል አትሌቲክስ የኢትዮጵያ ስም እና ዝና ከፍ እንዲል ያለው ሚና የጎላ መሆኑንና፣ በዓለም አደባባይ ኢትዮጵያ እንድትታወቅ በማድረግ ረገድ የምንኮራበት የስፖርት ዘርፍ እንደሆነ አንስተዋል ።
ክቡር ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል ፌዴሬሽኑ በሚያከናውናቸው የአገር ውስጥ ውድድሮች በፀጥታ ዘርፍ እንደ ከዚህ ቀደም ሁሉ አስፈላጊ ድጋፍ ከማድረግ ባለፈ “በሰንዳፋ ፓሊስ ኮሌጅ “የተቋቋመው የፎረንሲክ ላብራቶሪ የዶፒንግ ምርመራ በሃገር ውስጥ ለመጀመር በጋራ እንደሚሰራ እና ተቋማቸው ለአትሌቲክሱ እድገት የሚጠበቅበትን ሚና እንደሚወጣ ጠቁመዋል ።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን በበኩላቸው ፌዴራል ፖሊስ ለአትሌቲክስ ስፖርት እያደረገው ያለውን አስተዋጽኦ በማመስገን፣ አሁን የተጀመሩት መልካም እንቅስቃሴዎች ተጠናክሮ እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።
በውይይቱ ቀጣይ በአትሌቲክስ ስፖርት እና በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ “ጥናት” በሚፈልጉ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ በመነጋገር የመግባቢያ ሰነድ (MOU)ተዘጋጅቶ ለመፈራረም እቅድ ተይዟል ።
በመጨረሻም በርካታ ፣ስመጥር እና አንጋፋ የሃገር ኩራት የሆኑ አትሌቶችን ያፈራው “የኦሜድላ አትሌቲክስ ክለብ” በአትሌቲክሱ ልማት ላይ እያበረከተ ያለውን ድርሻ ተጠናክሮ እንዲቀጥል በጋራ እንደሚሰራ ስምምነት ላይ ተደርሷል።



B