የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን ዓድዋ ከተማ ገቡ::
የካቲት 21/2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን 20ኛው የኢትዮጵያ ማራቶን ሪሌ ውድድር ላይ ለመሳተፍ ዓድዋ ከተማ ገብተዋል ።
ፕሬዚዳንቱ አክሱም አፄ ዮሐንስ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል ።
የዓድዋ ከተማ ከንቲባ አቶ ተስፋይ ገብረውልድ እና ሌሎች የከተማ አመራሮች አቀባበል አድርጎላቸዋል ።
ከፕሬዚዳንቱ በተጨማሪ የፌዴሬሽኑ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ፣የማኔጅመንት አባላት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ዓድዋ ከተማ ገብተዋል ።




