###########################

ህዳር 29/2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በዓመት ውስጥ በእቅድ ይዞ ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል አንዱ የስፖርት ትጥቅ ድጋፍ ማድረግ ነው።

በዚህም መሰረት ፌዴሬሽኑ ለሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ስር ለሚገኙ ለሞሮቾ ፣አርቤ ጉና እና ሀገረ ሰላም የአትሌቲክስ ፕሮጀክቶች ድጋፍ አድርጓል ።

በሰዓቱ ተደረገው ጉብኝት ከአትሌቶች እና ከአሰልጣኞች በተነሳው ጥያቄ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን

እንዲሁም ከአቶ ወንድሙ ብሩ በሲዳማ ብ/ክ/መ/ ስፖርት ኮሚሽን የስፖርት አደረጃጀት ሀብት አሰባሳቢና የፋሲሊቲዎች ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ጋር ስለክልሉ የአትሌቲክስ እንቅስቃሴ እና በቀጣይ መንግስት ለክልሉ ፌዴሬሽን ማድረግ ስላለበት ድጋፍ ዙርያ ሰፊ ውይይት አድርገዋል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና ድሲፒሊንና ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶ/ር ትዕዛዙ ሞሴ ለአትሌቶች በጥሩ ድሲፕሊን በተገቢ እድሜ በመሰልጠን ነገ የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ በአለም አደባባይ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ የምታደርጉ መሆን አለባችሁ ብለው በመምከር ትጥቁን አስረክበዋል ።

የሲዳማ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ንጉሴ ወርቁ ፣ የሲዳማ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ለገሰ ለሚሶ ፣ የሲዳማ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አቃበ ነዋይ ሀይለአብ አሰፋ ፌዴሬሽኑ ላደረገውን ድጋፍ በማመስገን የስፖርት ትጥቁን ተረክበዋል ።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በሲዳማ ክልል ስር ለሚገኙ የአትሌቲክስ ፕሮጀክቶች ትጥቅ ድጋፍ አደረገ

Categories: Uncategorized