ህዳር 28/2018 ዓም

ትላንት ለሀገራች ዛሬ ለጤናችን እንሮጣለን በሚል በቀድሞ የኢትዮጵያ አትሌቶች ቡድን አዘጋጅነት በአንጋፋ አትሌቶች መካከል ዛሬ በወጣቶ ስፖርት አካዳሚ የደመቀ የአትሌቲክስ ውድድር ተካሄደ።

ውድድሩም በተለያየ የዕድሜ ደረጃ በ3ኪ.ሜትር ሴት በ5 ኪ.ሜትር ወንድ በሁለት ምድብ የተካሄደ ሲሆን የደከመን በመደገፍ እንደጥንቱ ወኔ እየተሰናነቁ ውድድሩን በደማቅ ሁኔታ ተፎካክረዋል ።

ከአንድ እስከ ሦስት አሽናፊዎች የሜዳልያ የገንዘብ ፤ ከአራት እስከ ሰባተኛ ለወጡት የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል ።

እንዲሁም ለቀድሞ አትሌት ኮማንደር ጌጤ ኡርጌ ከቀድሞ የኢትዮጵያ አትሌቶች ቡድን ለአቅም መዶጎሚያ ገንዘብ ተሰጥቷታል ።

✳️ አጠቃላይ ውጤት

በሴቶች ከ60 እሰከ 70 ዕድሜ

1 ፋንታዬ ሲራክ

2 ሰናይት ኃይሌ

በወንዶች ከ60 እሰከ 70 ዕድሜ

1 ተሰማ ያደቴ

2 ተስፋዬ ጣፋ

3 ስዩም ንጋቱ

በሴቶች ከ50 እሰከ 60 ዕድሜ

1 ታደለች ብራ

2 አዳነች ኤርቄሎ

3 አስረት ዳኜ

በወንዶች ከ50 እሰከ 60 ዕድሜ

1 ገመቹ ከበደ

2 ተገኑ አበበ

3 ማሞ ቀጄላ

🇪🇹‘በመደጋገፈ ጤናችንን እንጠብቅ’

🇪🇹ትላንት ለሀገራች ዛሬ ለጤናችን እንሮጣለን!

Categories: Uncategorized