ህዳር 01/2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ትናንት 43ኛው ጃንሜዳ ኢንተርናሽናል አቋራጭ ውድድር በታላቅ ድምቀት አካሂደዋል ።

በውድድሩ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የምስራቅ አፍሪካ አትሌቲክስ ዋና ፀሀፊ ዶክተር ሳዲቅ ኢብራሂም እና የታንዛኒያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዋና ፀሀፊ ጆን ማንያማ ውድድሩ አጠቃላይ የተካሄደበት አግባብ አድንቀዋል።

እንግዶቹ የተካሄደው ውድድሩ አስደናቂ እንደነበር ገልፀው፣በተጨማሪም የአደይአበባ ስቴዲየም ጎብኝተዋል።

የፌዴሬሽኑ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ዶክተር ትዕዛዙ ሞሴ፣ኢንስትራክተር አድማሱ ሳጂ፣አትሌት የማነ ፀጋይ እና የፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት ሀላፊ ዶክተር አመንሲሳ ከበደ ለዓመታት ከባድ ችግር የነበረውን የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ እና እየተሰራው ስላለው አዲሱ የአደይአበባ ስቴዲየም ሰፊ ማብራሪያ አድርጎላቸዋል ።

Categories: Uncategorized