የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አትሌቲክስ ፕሮጀክቶች ሱፐርቪዥን አካሄደ።

ሚያዝያ 07/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከሚያከናውናቸው የልማት ተግባራት አንዱ የሆነው፣የአትሌቲክስ ፕሮጀክቶች ሱፐርቪዥን በማድረግ አስፈላጊ የሙያ ድጋፍ ማድረግ ነው።

በዚህም መሰረት ፌዴሬሽኑ ወደ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በማቅናት ሚሻ (አትሌት ፋንቱ ሚጌሶ ፣ አትሌት በረከት ፣አሰልጣኝ ሰይፋ ነብሴ እና ሌሎች ያፈራ ) ፣ጉመር (አትሌት ሰለሞን ባረጋ ፣አትሌት ጥላሁን ሀይሌ ፣አትሌት አንዱአምላክ በልሁ እና ሌሎች ያፈራ እና አልቾ (አትሌት ሙክታር እንድሪስ ፣አትሌት አሊ አብዱልመናን ፣አትሌት ሳእዳ እና ሌሎች ያፈራ) ብዙ ታዋቂ አትሌቶች አገርን በመወከል በአህጉራዊ እና አለምአቀፋዊ ውድድሮች የተሳተፋ አትሌቶች ያፈሩ አትሌቲክስ ፕሮጀክቶች

ሱፐርቪዥን በማድረግ ሙያዊ ድጋፍ አድርጓል ።

የፌዴሬሽኑ የአትሌቲክስ ፋሲሊቲ ማህበራትና አትሌቶች አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ አሰፋ በቀለ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በመገኘት በሶስቱም አትሌቲክስ ፕሮጀክቶች ሱፐርቪዥን አከናውኗል ።

ዳይሬክተሩ በምልከታቸው በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የሚደገፉ 3 የአትሌቲክስ ፕሮጀክት መኖራቸው ፣አንዳንድ ፕሮጄክቶችን ወደ አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል ለማሳደግ ወረዳዎች ፣ ዞኖችና የልማት ማህበራት በጋራ የሚያበረታታ ስራ በመስራት ላይ መሆናቸውን ያነሱ ሲሆን፣ለሌሎች ክልሎች ጥሩ ተሞክሮ የሚሆን መሆኑን አንስተዋል ።

አቶ አሰፋ አክሎም፣ቀሪ ግንባታዎችና የአትሌቲክስ መሠረተ ልማት በማሟላት በሚቀጥለው በጀት ዓመት ወደ ተግባር እንቅስቃሴ የሚገቡ መሆኑ ጠቁመዋል ።

በሱፐርቪዥኑ ላይ ከአቶ አሰፋ በተጨማሪ አቶ ሰይፉ ዓለሙ የክልሉ ወጣቶችና ስፖርት ምክትል ቢሮ ኃላፊ ፣አቶ ማርቆስ ባሶሬ የክልሉ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ ፣የየዞኑ አመራሮችና ከተለያዩ ሴክተር ቢሮዎች የተወጣጡ የየወረዳው አመራሮች አሰልጣኞች ተገኝተዋል ።

Categories: Uncategorized, ዜና