ተጠባቂው የቶከዮ ማራቶን በኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸናፊነት ተጠናቀቀ ።
የካቲት 23/2017 ዓ.ም
የቶከዮ ማራቶን በሁለቱም ጾታ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በበላይነት አሸንፈዋል።
በወንዶች ታደሰ ታከለ ሲያሸንፍ በሴቶች ደግሞ አትሌት ሱቱሜ አሰፋ በበላይነት አሸንፋለች ።
በአለም አትሌቲክስ የፕላቲኒየም ደረጃ በተሰጠው ማራቶን በሴቶች አትሌት ሱቱሜ አሰፋ 2:16. 31 በመግባት በአንደኝነት አሸንፋለች ።
በወንዶች የቶክዮ ማራቶን አትሌት ታደሰ ታከለ በ2:03.23 በመግባት የግል ምርጥ ሰአቱን ጭምር በማሻሻል አሸንፈዋል ።
አትሌት ደረሳ ገለታ በ2 :03.51 በመግባት ሁለተኛ ደረጃ ይዞ አጠናቀዋል ።



