ጥቅምት 22/2018 ዓ.ም
በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ሲካሄድ የቆየው 2ኛው የኢትዮጵያ ወጣቶች ኦሎምፒክ ጨዋታዎች የአትሌቲክስ ውድድር ዛሬ ፍፃሜውን አግኝቷል ።
ከጥቅምት 19-22/2018 ዓ.ም የተካሄደው ውድድር በኦሮሚያ ክልል አጠቃላይ አሸናፊነት ተጠናቀዋል ።
በውድድሩ ኦሮሚያ ክልል በ19 የወርቅ፣ 12 የብር እና 10የነሀስ ሜዳልያዎች በአንደኝነት ሲያጠናቅቅ ፣አዲስአበባ በ8 የወርቅ ፣9 የብር እና 4 የነሀስ ሜዳልያ ሁለተኛ እንዲሁም ትግራይ 1የወርቅ፣ 3 የብር እና 5 የነሀስ ሜዳልያ በማግኘት ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድራቸውን አጠናቀዋል ።
“የወጣቶች ኦሊምፒክ ውድድር ለሀገር ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል ከጥቅምት 15 እስከ 23/ 2018 ዓ.ም የተካሄደው 2ኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ ጨዋታዎች ነገ በአዲስ አበባ ስቴዲየም የመዝጊያ መርሀግብር ይከናወናል ።