ታሕሣሥ 05/2018 ዓ.ም

በመቐለ ከተማ ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደው የ1ኛው የኢትዮጵያ 10 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ ።

የዚህ ውድድር ዓላማ ለክልልና ከተማ አስተዳደር፣ ክለብ ፣ተቋማትና፣ የግል ተወዳዳሪ አትሌቶች የውድድር ዕድል ለመፍጠርና ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት እንዲሁም አትሌቶችን በሽልማት ለማበረታታት ነው ።

በዚህ ውድድር የተገኙት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ጽ/ቤት ሃላፊ ዶ/ር አመንሲሳ ከበደ እንደገለፁት :- እንደዚህ አይነት ውድድር መቐለ ከተማ መካሄዱ በክልሉ ላሉት አትሌቶች ፣ክለቦች እና ለከተማው መነቃቃትን የፈጠረና የስፓርት ማህበራትን ያሰባሰበ ከመሆኑ ባሻገር ማህረሰቡን በማቀራረብ የከተሞችን ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ

መነቃቃት የሚያሳድግ ነው ።

አክለውም እንደዚህ አይነት ውድድር ፓለቲካዊ ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳው የጐላ በመሆኑ በዚህ መሰረት በቀጣይ ይህንን መሰል ውድድር በባህር ዳር እና በሀዋሳ ከተሞች የሚደረግ መሆኑን በመግለጽ እንደዚህ ያሉ ውድድሮችን እስፓንሰር በማድረግ ለአትሌቲክስ እድገት አብረውን መስራት ለሚፈልጉ ፌዴሬሽናችን በሩ ክፍት ነው ብለዋል ።

Categories: Uncategorized