ታህሳስ 01/2018 ዓ.ም

በአሜሪካ ፍሎሪዳ በሚካሄደው 46ኛው የዓለም አገር አቋራጭ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ዛሬ በሱሉልታ የተለያዩ ስልጠናዎች ተሰጥቷል ።

ቡድኑ ሜዳ ላይ ከሚያደርገው ዝግጅት ጎን ለጎን የስነ ልቦና ስልጠናዎች በተለያዩ ባለሙያዮች እየተሰጡት ነው።

አሸናፊ ስነ ልቦና እንዴት መግንባት እንደሚቻል እና የቡድን ትስስር እና ስሜት ግንባታ በተመለከተ በኢንስትራክተር መሰረት መንግስቱ ጥልቅ የሆነ ስልጠና ተሰጥቷቸዋል ።

የውድድሩ ቡድን መሪ እና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ወ/ሮ ሳራ ሃሰን አትሌቶቹ አውንታዊ አመለካከት በማሳደግ እና የቡድን ቁርጠኝነት ማጎልበት እንደሚገባቸው ተናግረዋል ።

አትሌቶች አውንታዊ ሆነው እርስ በእርስ መማማር እና መደጋገፍ እንደሚገባቸው ወይዘሮ ሳራ በስልጣናቸው ላይ አንስተዋል ።

የኢትዮጵያ አትሌቶች ማህበር ፕሬዚዳንትና የፌዴሬሽኑ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ሌተናል ኮነሬል አትሌት የማነ ፀጋይም በበኩላቸው ከዚህ በፈት ያካበቱትን ልምድና ተሞክሮ በመድረኩ ለአትሌቶቹ አካፍለዋል ።

Categories: Uncategorized