በራሳችሁ ተማመመኑ ፣አገርን አስቀድሙ፣በቡድን ስሩ፣ ያላቹን አቅም እወቁ ከዛ ማሸነፍ ትችላላችሁ” :-አትሌት ቀነኒሳ በቀለ
የዓለም አገር አቋራጭ ንጉሱ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በ46ኛው የዓለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮና ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ሱሉልታ በመገኘት በዓለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮና ውጤታማ የሆነበትን የራሱን ልምድ አካፍለዋል ።
ኢትዮጵያን በተለያዩ ዓለም አቀፍ ውድድሮች 43 ጊዜ በመወከል ቀዳሚ የሆነው እና ኬንያውያን አትሌቶች ነግሰውበት የነበረው የዓለም አገር አቋራጭ ታሪክ ወደ ኢትዮጵያ የመለሰው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በ46ኛዉ የዓለም ሀገር አቋራጭ ዉድድር ላይ ለሚሳተፉ አትሌቶች አገርን የመወከል ሀላፊነት በተመለከተ ሰፊ ተሞክሮውን አካፍሏል ።
አትሌት ቀነኒሳ በውድድሩ ተካፋይ የሆኑ አትሌቶች አገርን በማስቀደም የቡድን ስራ ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ የገለፀ ሲሆን፣”በራሳችሁ ተማመኑ፣አገር አስቀድሙ፣ በደንብ ልምምድ ስሩ ፣ያላችሁን አቅም እወቁ ከዛ ማሸነፍ ትችላላችሁ” ሲልም ተናግሯል ።
አትሌት ቀነኒሳ በቀለ 25 አመታትን ባስቆጠረው የአትሌቲክስ ሕይወቱ በዓለም የሀገር አቋራጭ ውድድር 11 ወርቅ እና 1 የነሃስ ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ አስገኝቷል።
የ43 አመቱ አትሌት ቀነኒሳ አገርን በወከላባቸው ውድድሮች በአጠቃላይ 34 ሜዳሊያዎችን አሸንፏል ።
አትሌቶቹም በዓለም አገር አቋራጭ ንጉሱ አትሌት ቀነኒሳ ገለፃ ፣ልምድና ተሞክሮ መደሰታቸውን ገልፀዋል ።





