ሕዳር 27/2018 ዓ.ም

የፔፕሲ አዲስ አበባ የክለቦች አቋም መለኪያ ውድድር በ2014 ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን ዘንድሮ ለአምስተኛ ግዜ በወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ከህዳር 25_28/2018 ዓም ጀምሮ እየተካሄደ ይገኛል።

በአጭርና መካከለኛ ርቀትና በውርወራ ተግባራት ባጠቃላይ በ25 የውድድር አይነቶች ለአራት ቀናት ያህል ይካሔዳል።

በውድድሩ ከ18 ክለቦች የተውጣጡ 228 ወንድና 142 ሴት በድምሩ 370 አትሌቶች እየተፎካከሩ ሲሆን በውድድሩ ለሚያሸንፉ አትሌቶች የሜዳሊያ ሽልማትና በአጠቃላይ ውጤት ለሚያሸንፉ ክለቦች የዋንጫ ሽልማት መዘጋጀቱ ታውቋል።

ውድድሩ በየአመቱ የሚካሔድ ሲሆን ክለቦች አቋማቸውን በመፈተሽ በቀጣይ የሻምፒዮናና ሀገራዊ ውድድሮች ላይ ጠንካራ ተፎካካሪ ለመሆን የሚያስችላቸው እንደሆነ ይታመናል።

በዛሬ ቀን የተካሄዱት የፍፃሜ ውድድሮች

✳️ ከፍታ ዝላይ በሴቶች

በፀሎት አለማየሁ መቻል 1.55

ሣራ ኛኞው መቻል 1.55

ዊዲ ኡባንግ መቻል 1.50

✳️ ከፍታ ዝላይ ወንዶች

ማል ጎኝ ኢ/ኤሌትሪክ 2.00

ኦኮሎ ኡጁሉ መቻል 2.00

ለም ቢኮድ መቻል 1.90

በነገው ዕለት ውድድሩ ፍፃሜውን የሚያገኝ ይሆናል።

Categories: Uncategorized