11 የክልሉ ዞኖችና የአትሌቲክስ ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበትን የሶማሌ ክልል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የ1ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ዋና ከተማ በሆነችው በጂግጂጋ ከጠዋቱ 2:00 ጀምሮ በተሳካ ሁኔታ አካሄዷል ።
በጉባኤውም መጀመርያ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር እና የ2017 ዓ.ም የክልሉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሪፖርት በፌዴሬሽኑፕሬዚዳንት አቶ አብዲቃድር ሙሁመድ አብዲ የቀረበ ሲሆን የክልሉ ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ ዋና ሃላፊ አቶ መሀመድ መሀዲን እና የክልሉ ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ የስፓርት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሃላፊ አቶመሀመድ አብዱራህማን በየተራ የክልሉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በበጀት አመቱ ያከናወናቸውን ተግባራቶች በማበረታታት እና በማመስገን እንዲሁም ሌሎች የስፖርት ማህበራት ጉባኤያቸውን በዚህ መልኩ ማካሄድ እንደሚገባቸው ገልፀዋል ።
በቀረበው ሪፓርት እና በቀጣይ በሚኖረው ስራ ላይ ከጉባኤው ተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት የተካሄደ ሲሆን ከተሳታፊዎቹም ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተዋል በተነሱት ጥያቄዎች ዙሪያ ከመድረኩ ምላሽ ተሰጥቶ ጉባኤው ከረፋዱ 11:00 ተጠናቋል ።



