የአዲዳስ ካምፓኒ ማርኬቲንግ ማኔጅመንት ተወካይ ዳኒኤል ሎቤ በአዲስአበባ
#############################
የካቲት 6/2018 ዓ.ም
የአዲዳስ ካምፓኒ የሩጫ ማርኬቲንግ ማኔጅመንት ተወካይ ዳኒኤል ሎቤ ዛሬ ጠዋት አዲስ አበባ ገብተዋል።
በዓለም አትሌቲክስ እውቅና ያገኘው የአደይ አበባ ዓለም አቀፍ የመለማመጃ ትራክ ፣ በመገባደድ ላይ የሚገኘውን ስቴዲየም እና የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ጎብኝተዋል።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጽ/ቤት ሀላፊ ዶክተር አመንሲሳ ከበደ ቦሌ አለምአቀፍ አየር ማረፊያ አቀባበል ያደረጉላቸው ሲሆን፣ በጉብኝታቸው ላይ ማብራሪያ አድርጎላቸዋል ።
ጉብኝታቸው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የጀመረውን ዓለምአቀፍ የአትሌቲክስ ስፖርት ዲፕሎማሲ ግንኙነት የሚያጠናክር እንደሆነ ተመላክቷል።
የዓለም አትሌቲክስ የውደድር ዋና ዳይሬክተር ፒርስ ኦክሎጋን በአዲስአበባ የነበራቸው ቆይታ ፣ውጤታማ እንደነበር የሚታወስ ነው።




