“ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ውድድር የማዘጋጀት ሙሉ አቅም አላት” :-የዓለም አትሌቲክስ የውድድር ዋና ዳይሬክተር ፒርስ ኦክላጋን
የካቲት 3/2018 ዓ.ም

የዓለም አትሌቲክስ የውድድር ዋና ዳይሬክተር ፒርስ ኦክላጋን ዛሬ ጠዋት አዲስአበባ መግባታቸው የሚታወቅ ነው።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ባደረገላቸው ግብዣ መሠረት አዲስአበባ የገቡት ዳይሬክተሩ፣ በዓለም አትሌቲክስ እውቅና ያገኘው የአደይአበባ ዓለምአቀፍ የመለማመጃ ትራክ እና በመገባደድ ላይ የሚገኘውን ስቴዲየም በከስዓት መርሀግብር ጎብኝተዋል።

ዳይሬክተሩ ኢትዮጵያ የጀግኖች አትሌቶች መፍለቂያ ናት ያሉ ሲሆን በመገባደድ ላይ የሚገኘው አደይ አበባ ዓለም አቀፍ ስቴዲየም ከጎበኙ ብኃላ” ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ እና አህጉር አቀፍ ጨምሮ የተለያዩ ውድድሮችን የማዘጋጀት ሙሉ አቅም አላት” ብዋሏል።

ዳይሬክተሩ አክሎም የተሰሩ የአትሌቲክስ መሰረተ ልማቶች ካደነቁ ብኋላ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ወደ ከፍታ ለማምጣት ሁለንተናዊ ድጋፍ ክትትል እንደሚያደርጉ ጠቁመው ፣

በቀጣይም ጊዜውን የሚፈልገው ብቁ የአትሌቲክስ የሰው ሀይል ማደራጀት እና

የስፖርት ቴክኖሎጂ ማጎልበት ላይ ፌዴሬሽኑ አበክሮ መስራት እንዳለበት አንስተዋል ።

Categories: Uncategorized