ታላቅ ምስጋና !
የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ልዩ ትኩረት ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ትንሳዔ !
በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በስፖርቱ ዘርፍ በተለይም በአትሌቲክሱ የሰጡት ትኩረት እና በሳል አመራር የአትሌቲክሱን ስብራቶች እየጠገነ ይገኛል ።
ዛሬ በአዲስ ስፖርት ፓርክ በኦሎምፒክ መድረክ ለሀገራችን የወርቅ ሜዳሊያ ላስገኙ የ15 አትሌቶቻችን የክብር ሐውልቶችን ደግሞ አንደኛው ማሳያ ተደርጎ ይቆጠራል ።
ይህም የትላንት ጀግኖችን በመዘከር ቀጣዩን የአገር ተረካቢ ትውልድ በአገር ፍቅር ስሜት ለመገንባት ትልቅ ሚና ይጫወታል።
በኦሎምፒክ መድረክ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ከፍ ላደረጉ አትሌቶችን የሚዘክሩ የክብር ሐውልቶች መቆማቸው፤ የጀግኖቻችንን ታሪክ ሕያው ከማድረግ ባለፈ ለቀጣዩ ትውልድ ስፖርተኞች ታላቅ ተምሳሌት ይሆናሉ።
በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር የላቀ ቁርጠኛ አመራር ለበርካታ አመታት የአትሌቲክሱ ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ እየተፈቱ ይገኛሉ።
በአዲስ አበባ ብቻ የአደይ አበባ ዓለምአቀፍ ስታዲየም የመለማመጃ መም ፤ የአዲስ አባባ ስታዲየም መም እና በቅርቡ የሚጠናቀቁት የአደይ አበባ እና የአቃቂ ስታዲየም ግንባታዎች ትውልድ ተሻጋሪ እና ታሪክ የሚዘክራቸው ናቸው።
በስፖርት ዲፕሎማሲ እና በውጭ ግንኙነት ከዓለም አትሌቲክስ ጋር በተፈጠረው መልካም ግንኙነት ኢትዮጵያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ የዓለም አትሌቲክስ ኮንቲኔንታል ቱር እንድታስተናግድ መመረጧ ታሪካዊ ድል ነው።
በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እየተሰሩ የሚገኙ ስራዎች የኢትዮጵያ አትሌቲክስን በአገር ውስጥና በአለም አቀፍ ደረጃ ተፎካካሪ እና አሸናፊ ሀገር ለመገንባት የማይተካ ሚና ይኖረዋል።
የአዲስአበባ ከተማ ከንቲባ ክብርት ወይዘሮ አዳነች አበቤ በተጨማሪም ለአትሌቲክሱ ልዩ ትኩረት በመስጠት ፣ በተለያዩ የአትሌቲክስ መድረኮች የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓለማ እንዲውለበለብ ያደረጉ አንጋፋ አትሌቶቻችን ባሳለፍነው ወር በመደገፍ ያሳዩት ቁርጠኝነት ፌዴሬሽናችን ማመስገን ይፈልጋል ።
ክብርት ከንቲባችን በከተማዋ እየተገነቡ ያሉትን የአትሌቲክስ መሰረተ ልማቶች እንዲፋጠኑ ላደረጉት አስተዋጽኦ ምስጋናችን የላቀ ነው።
ፌዴሬሽናችን መንግስት ለአትሌትክሳችን እድገት የሚያደርገውን ሁለንተናዊ ድጋፍ እና ክትትል በማመስገን ሚያዚያ 10/2018 ዓ.ም ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የምታስተናግደውን ዓለምአቀፍ የአንድ ቀን ውድድር በከፍተኛ ስኬት ለማጠናቀቅ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቃችን በዚሁ አጋጣሚ እየገለጽን አትሌትክሳችን ወደ ነበረበት ከፍታ ለመመለስ ተግተን እንሰራለን ።








