በአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር ለሚገኙ የአትሌቲክስ አሰልጣኞቾ የሙያ ማሻሻያ ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ
###########################
ታህሳስ 13/2018 ዓ.ም
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከአዲስአበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር በአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ለሚገኙ የአትሌቲክስ አሰልጣኞች እና ዳኞች የሙያ ማሻሸያ ሲሰጥ የቆየውን ስልጠና አጠናቀቀ።
በስልጠናው በርካታ ሴቶች ሰልጣኞች ተሳትፈዋል።
የአትሌቲክስ አሰልጣኞች ስልጠና በዶ/ር ብዙአየሁ ታረቀኝ እና መሪ ኢንስትራክተር ፍቃዱ ከበደ ሰጥተዋል።
በሌላ መልኩ በአሰልጣኝ ጌታሁን ስለሺ እና በአሰልጣኝ ታደሰ ጌታነህ የአትሌቲክስ ዳኞች ስልጠና ተሰጥቷል።
በአራት ኪሎ ስፓርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል(ወወክማ) ሲሰጥ በነበረው ስልጠና 74 የአትሌቲክስ አሰልጣኞች እና 100 የአትሌቲክስ ዳኞች ስልጠናውን ተካፍለዋል።
የሙያ ማሻሻያ ስልጠናውን በአግባቡ በመከታተል ላጠናቀቁ ስልጣኞቸ በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እና በአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የምስክር ወረቀት ተበርክቷል።


