በናይጄሪያ የተሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ደማቅ አቀባበል ተደረገለት።

##########################

የካቲት 30/2018 ዓ.ም

በቦትስዋና ጋቦሮኔ ከሜይ 2-3/2026 የሚካሄደውን የዓለም የአትሌቲክስ ሪሌ ውድድር ለመሳተፍ የሚያስችል ስዓት ለማምጣት በናይጄሪያ የተወዳደረው

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ቡድን ዛሬ ጠዋት አዲስአበባ ገብተዋል ።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት በማርዮት ሆቴል ደማቅ አቀባበል አድርጎላቸዋል ።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን ከናይጄሪያ ካላባር ለተመለሰዉ የልዑክ ቡድን የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር አድርገዋል።

በንግግራቸዉም በአጭር ጊዜ ተሰባስባችሁ ላስመዘገባችሁት ዉጤት እናመሰግናለን በማለት ከሰራን እንደምንችል ዉጤቱ መልካም ጅማሮ ማሳያ መሆኑን ገልፀዋል።

በየክለቦቻችሁ ጥሩ ዉጤት እና ስራ ስለሰራችሁ ስራ አስፈፃሚዉ ወስኖ በአጭር ጊዜ ይህንን ዕድል እንድታገኙ አድርጓል ብሏል።

በቀጣይ እንደ ተቋም ጥሩ ግንኙነት ከናይጄሪያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጋር ስለተፈጠረ ወደፊት የተሻሉ

ብዙ ስራዎች አብረን የምንሰራ ይሆናል ሲሉም ፕሬዚደንቱ የገለፁ ሲሆን አጭር ርቀት ላይ በዲሲፒሊን የታነፀ አትሌት ማፍራት እንደሚገባ አሳስበዋል ።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ኢንጅነር ጌቱ ገረመው በበኩላቸው

የመጣው ውጤት ጥሩ መሆኑንና ፣ በቀጣይ በ2028 ለሚካሔደዉ የሎሳንጀለስ ኦሎምፒክ ላይ በእናንተ ተስፋ አለን ሲሉ ተናግሯል ።

በሚቀጥለዉ አመት በተደራጀ መልኩ ለአጭር ርቀት ልዩ ትኩረት ሰጥተን እንሰራለን በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል።

ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዜዳንቱ በተጨማሪም ለልዑክ ቡድኑ ባልተለመደ ሁኔታ ልዩ ትኩረት የተሰጠዉ የአጭር ዕርቀት በአጭር ጊዜ ዝግጅት ይሄ ውጤት ካስመዘገባችሁ

በደንብ ካገዝናችሁ ከዚህ የተሻለ ዉጤት ማምጣት እንደምትችሉ አሳይታችዋሉ ያሉ ሲሆን ፌዴሬሽኑ በትኩረት እንደሚሰራ አንስተዋል ።

በአቀባበል መርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ፣ኢንስትራክተር አድማሱ ሳጂ፣ዶክተር ትዕዛዙ ሞሴ

እና አትሌት በላይነሽ ኦልጅራ ቡድኑ በአጭር ርቀት ላይ ባስመዘገበዉ ዉጤት የተሰማቸውን ደስታ በመግለፅ ወደፊት ብዙ መስራት እንዳለብን አመላካች ነው ያሉ ሲሆን ፣በሌሎች የሜዳ ተግባራት መስራት የሚያስፈልግ መሆኑን አንስተዉ የመጣዉ ዉጤት ለቀጣይ ብዙ ትምህርት ሰጪ መሆኑን ገልፀዋል።

የቴክኒክ ቡድን መሪ አትሌት አሸብር ደምሴ፣አሰልጣኝ ጌታቸው ሙሉጌታ ፣አትሌት መርዶክዮስ ወልዴ እና አትሌት አጃይባ አሊዩ በናይጄሪያ የነበራቸውን ቆይታ በማብራራት በተለይ ፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት የውድድር እድልን መፍጠርን ጨምሮ ሁሉም አስፈላጊ ድጋፍ ስላደረገላቸው አመስግነዋል ።

ቡድኑ በውድድሩ በ400 ሜትር ወርቅ፣በሴቶች 400 ሜትር ብር እና በወንዶች 400 ሜትር ነሀስ በቡድን ማስመዝገቡን የሚታወስ ነው።

Categories: Uncategorized