በ24ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ 15 ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ አጠናቀቀች ።
በጋና አስተናጋጅነት ሲካሄድ የቆየው 24ኛው የአፍሪካ ሲኒየር አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ሲጠናቀቅ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአጠቃላይ 15 ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ ውድድሩን በድል አጠናቋል።
በዚሁ ታላቅ አህጉራዊ መድረክ ላይ ሀገራችንን ወክለው የገቡ አትሌቶች በኩራት የኢትዮጵያን ባንዲራ ከፍ ማድረግ ችለዋል።
በውድድሩ አትሌት አጃይባ አልዩ ፣ አትሌት ምስጋና ኃይሉ፣ አትሌት ገመቹ ጎዳና ፣አትሌት ምስጋናው ዋቁማ እና አትሌት ውብአለም ሽጉጤ የወርቅ ሜዳሊያ አሸንፏል።
የ4 በ 400 ሜትር የሴቶች ሪሌ ቡድን ፤ አትሌት ኦታጌ ኦባንግ፣አትሌት ሙቢን ሀጂ እና አትሌት ሀጎስ እዮብ የብር ሜዳሊያ ስኬት ያስመዘገቡት አትሌቶችናቸው።
የነሐስና የክብር አሻራ ያሳረፉት ቀሪዎቹ ስኬታማ አትሌቶች ደግሞ አትሌት አልማዝ፣ አትሌት ሳሙኤል ፍሬው፣ አትሌት ዝይን አየልኝ፣ አትሌት በፀሎት አለማየሁ፣ አትሌት አሰፉ አብርሃ እና አትሌት አብዱልሰላም አብዱልዋሂብ ናቸው።
ኢትዮጵያ በዚህ ታላቅ የአህጉሪቱ የስፖርት መድረክ ላይ በ32 ሴት እና በ31 ወንድ አትሌቶች፣ በአጠቃላይ 63 አባላት ያሉት ጠንካራ ልዑክ በማሳተፍ ደማቅ ተሳትፎ አድርጋለች።
የተመዘገበው ስኬትም የኢትዮጵያን የአትሌቲክስ የበላይነት በአህጉሪቱ መድረክ ዳግም ያስመሰከረ ሆኗል።








