የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስፖርት ትጥቅ በየአመቱ ለታዳጊ የፕሮጀክት አትሌቶች እንደሚያከፋፍል ይታወቃል፡፡

ዶ/ር ትዕዛዙ ሞሴ ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የዲሲፒሊንና ቅሬታ ሰሜ ኮሚቴ ሰብሳቢ እና አቶ ቶሎሳ ጅጆ የፌደሬሽኑ የሪክርድና ማህደር ባለሙያ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አቶ ኢብራሂም መንሱር የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር፣ አቶ አስማማው አዲሱ በኮሚሽኑ የማህበራት ማደራጃ ዳይሬክተር፣ አቶ አጠይብ መሀመድ በኮሚሽኑ የስልጠናና ውድድር ዳይሬክተር፣ አቶ አላዛር ፀሐይ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጽ/ቤት ኃላፊ እና ወ/ሮ ምርቴ ምትኩ በኮሚሽኑ የስፖርት ትጥቅ ማደራጃ ባለሙያ እና የፌደሬሽኑ ስራ አስፈፃሚ አባላት በዕለቱ በተገኙበት ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ በመተከል ዞን ለወንበራ ዕዉቀት ጮራ አትሌቲክስ ፕሮጀክት ጣቢያ በመሰልጠን ላይ ላሉ ለ30 ታዳጊ ፕሮጀክት አትሌቶች(11 አይነት የስፖርት ትጥቅ አልባሳት) ለ 2 አሰልጠኞች እንዲሁም ለ14 የባለድርሻ አካላት በቀን 22/04/2018 ዓ. ም ርክክብ አድርገዋል፡፡

ከርክክቡ በኋላ ስለ ዓመቱ የትጥቅ ስርጭትና ሱፐርቪዝን፣ የፕሮጀክቱ አሁናዊ ሁኔታው እና በአጠቃላይ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአትሌቲክስ ስፖርት ልማት ላይ ሰፋ ያለ የጋራ ውይይት ተደርጓል፡፡

በዚህም ረገድ ከክልሉ የፌደሬሽንና ከኮመሽኑ አመራር አካላት በኩል ክልሉ በራሱ አቅምና ተነሳሽነት ፈርጀ ብዙ ስራዎችን በመስራት ላይ እንዳለና በተለይ በአትሌቲክስ ስፖርት እንደሀገር ብዙ ስራ በመስራት ላይ እንዳሉ ገልፀው፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽኑን የስራ አስፈፃሚ አባላትን አሶሳ ድረስ ልኮ በዚህ ልክ የትጠቅ ስረጭት ለታዳጊ አትሌቶቻችንና የስራ ሱፐርቪዥን ስራን የጋራ አድረጎ ተግባብቶ ለመስራት በመቻሉ አቶ ኢብራሂም መንሱር የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አድናቆታቸውን ገልፀዋል፡፡

አቶ አላዛር ፀሐይ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጽ/ቤት ኃላፊ አክለውም በዚህ ዓመት የታዳጊ አትሌቶች የማልማት ስራዎች አቅም በፈቀደ መጠን እየሰራን ነው ቢሆንም አሁንም ድጋፍ ያስፈልገናል ያሉ ሲሆን፣ የፕሮጀክት ጣቢያው በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝና በብዙ ጉዳዮች በትብብር መስራት እንደሚያስፈልግ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡

ከተነሱ ጥያቄዎች መካካል የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካበረከታቸው ጀግኖች አትሌቶች (አልማዝ አያና፣ ጽጌ ድጉማ፣ አለም ፀሐይ ገመቱ እና ሌሎችም) አንፃር በሚገባው ልክ ያልተዘመረለት ሆኖ ለብዙ ዓመታት የፕሮጀክት ጣቢያ የይጨመርልን ጥያቄውን በተለያዩ መድረኮች ብናነሳም አስካሁን ድርስ 1(አንድ) የታዳጊ ፕሮጀክት ጣቢያ ብቻ አነስተኛ ነው ሲሉ አቅርበዋል፡፡

ዶ/ር ትዕዛዙ ሞሴ የፌደሬሽኑ ዋናና ተቀዳሚ ስራው አድርጎ እየሰራ ያለው ከጥቂት ጊዜ ወዲህ የጠፋውን አትሌቲክሰችንን ፍለጋ ላይ በመሆኑ ይህ ደግሞ የሚሳካው ከታች ታዳጊ ጀምሮ ጠንክሮ በጋራ መስራት ስለሆነ ለጥያቄው መልስ እንዲያገኝ ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ስራ አስፈፃሚ አባላት በጽ/ቤቱ በኩል እንደሚቀርብና መፍትሄ የሚያገኝ መሆኑን በመግለጽ ለአብነት የሚሆን ስራ በ2018 ዓ.ም ለሙከራ የሚሆኑ የትምህርት ቤት ኪድስ አትሌቲክስ ስልጠና ጣቢያዎችን መጀመራችንንና ይህ ክልልም ልዩ የተፈጥሮ ችሎታ ባላቸው አካባቢዎች ልየታ ቢደረግና እንደ ሞዴል እንዲሆኑ በማድረግ በዚህም ረገድ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ለኮሚሽን አመራሮችና ለፌደሬሽን ስራ አስፈፃሚ አባላት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የክልሉ አመራሮች የአትሌቲክሱን ጣዕም ስላወቁ ለአትሌቲክሱ ልዩ ተሰጥዖ ያለው ክልል በመሆኑ ብዙ ታዳጊዎችና ክለቦች እንዲኖሩት ቀጥሎም ጥሩ የሆኑ ውድድሮችን በማዘጋጀት አግባብነት ያለው የመስራት ፍላጎት እንዳላቸው በጥልቀት የስራ ዕቅዳቸውን በማካፈል ፌዴሬሽኑ ትብብሩ ከጎናቸው እንዳይለያቸው በአጽኖት እየጠየቁ ከወተሮው ለየት ባለ መልኩ ብዛት ያለው ትጥቅ ስለተበረከተ አቶ ኢብራሂም መንሱር የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር በክልሉና በፌደሬሽኑ ስም ምስጋናቸውን ከልብ አቅርበዋል፡፡

በመጨረሻም የኢትዮጵያ አትሌቲክስን ወክለው አሶሳ ከተማ ድረስ ለመጡ ለዶ/ር ትዕዛዙ ሞሴ እና ለአቶ ቶሎሳ ጅጆ በጋራ የመስራት ባህላችን ከዚህ በበለጠ እንዲጨምር አደራ በማለት የክልሉን ባህላዊ ልብስ አቶ ኢብራሂም መንሱር በክልሉ ስፖርት ኮሚሽን እና በፌደሬሽኑ ስም አበርክተዋል፡፡

Categories: Uncategorized