ፌዴሬሽኑ የሪፎርም ተግባሩ አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል

#

ጥቅምት 12/2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የተጀመረውን ሁለንተናዊ ተቋማዊ ለውጥ ተግባር አጠናክሮ ቀጥለዋል።

በዚህም መሰረት የፌዴሬሽኑ የሪፎርም ተግባሩ ከሚመሩ ከዩኒቨርስቲ ሙሁራን ፣ከክለብ አሰልጣኞች ፣የዳበረ ልምድ ካላቸው የብሄራዊ ቡድን አሰልጣኞች፣ ከአካዳሚ ባለሙያዎች እና ከተለያዩ ተቋማት የተወጣጡ የአትሌቲክስ ከፍተኛ ባለሙያዎች ዘጠኝ አባላትን ( ዶ/ር ከሳቴ ለገሰ መቀለ ዩኒቨርስቲ ፣ዶ/ር ዘሩ በቀለ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፣ዶ/ር አበራ ደሳለኝ ኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ፣ዶ/ር አበራ አሰፋ ኮተቤ ዩኒቨርስቲ ፣
ሻምበል ቶሎሳ ቆቱ አሰልጣኞች ማህበር መከላከያ ክለብ፣ኢንስፔክተር አክሊለ ፣ መሠረት መንግስቱ ሰላሌ ዩኒቨርስቲ ደራርቱ አካዳሚ፣ መላኩ ደረሠ አሰልጣኝ ፣ገብረሚካኤል ተክላይ ትግራይ አሰልጣኝ) ያካተተ ኮሚቴ ጋር ውጤታማ ውይይት አድርገዋል ።

በውይይቱ ላይ በሪፎርም ንድፍ ሀሳብ አስፈላጊነት ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን በለውጥ ትግበራ መነሻነት የአደረጃጀት፣ስትራቴጂክ ፕላንና፣ የመዋቅር ፣ ደንብን ጨምሮ ልዩ ልዩ የአሰራር፣የህግ ማዕቀፎች ፣የባለሙያነት አቅም ፣የመልካም አስተዳደር ቻርተር ለማዘጋጀት የሚያስችል ነው።

በአጠቃላይ የአትሌቶች ስልጠና፣ ብቃት ማዕቀፍ ከብሄራዊ ቡድን ሳይንሳዊ ስልጠና፣ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የአደረጃጀት እና ደንብ አሰራር ኑሮት እንዲዘምን ተደርጎ የሚሰራ ይሆናል።

በተጨማሪም የአገር ውስጥ ውድድሮች ደረጃቸውን ከፍ እንዲሉ እና እድሎችን ማስፋት ያተኮረ ፣አለምአቀፍ ውድድሮች በአገር ውስጥ እንዲካሄድ ማድረግ ላይ አተኩሮ እንደሚሰራ ተጠቁመዋል

በመጨረሻም በውድድሮች የአትሌቲክሱ ገፅታ ግንባታ አተኩሮ እንዲሰራ አቅጣጫ በማስቀመጥ የሪፎርም ተግባሩ በሁለት ወራት ውስጥ እንዲጠናቀቅ የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ ውይይቱ ተጠናቀዋል ።

በውይይቱ ላይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን፣የፌዴሬሽኑ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ኢንጅነር ጌቱ ገረመው እና የፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት ሀላፊ ዶክተር አመንሲሳ ከበደ ተገኝተዋል ።

Categories: Uncategorized