ኢትዮጵያ በታላቅ የታሪክ ስኬት የምትታወቅበት ተቋም በመግባቴ ደስታ ተሰምቶኛል፣ለውጥ ለማምጣት እሰራለሁ” :- ዶክተር አመንሲሳ ከበደ

#

መስከረም 26/2018 ዓ.ም

“እንደ አገር የምንመካበት እና በታላቅና ደማቅ የስኬት ታሪክ የምንታወቅበት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቋም ውስጥ በመግባቴ ደስታ ተሰምቶኛል “ያሉት አዲሱ የፌዴሬሽኑ የጽ/ቤት ሀላፊ ናቸው።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትና ሰራተኞች ለፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት ሀላፊ ዶክተር አመንሲሳ ከበደ ደማቅ አቀባበል አድርጎላቸዋል ።

ዶክተር አመንሲሳ በተቋሙ ለውጥ ለማምጣት እንደሚጥሩና አሁን ያለው ስራ አስፈፃሚ ለለውጥ ዝግጁ በመሆኑ በጋራ ተቋማዊ ጥንካሬን በማምጣት፣ያለኝን ልምድና መልካም የአትሌቲክስ ተሞክሮ በመጠቀም የነበረውን የአትሌቲክሱ ከፍታ ለመመለስ እንደሚሰሩ ተናግሯል ።

የፌዴሬሽኑ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትና ሰራተኞች መልካም ምኞታቸውን ገልፀውላቸዋል

መልካም የስራ ዘመን !

Categories: Uncategorized